በኦሮሚያ የህግ የበላይነት ለማስከበር ዓውደ ጥናት ተደረገ

Posted: October 17, 2011 in Uncategorized

(ቢሊሱማ, ጥቅምት 17 ቀን 2011) – የህግ የበላይነት ለማክበርና ለማስከበር ለሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት ስኬት ከፍትህ አካላትና ከህግ ባለሙያዎች ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ አስታወቁ።

የኦሮሚያ ጠበቆች ማህበር ለኦሮሚያ ክልል ጠበቆች ያዘጋጀው ዓውደ ጥናት አደስ አበባ ውስጥ ዛሬ ተጀምሯል።

ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ዓውደ ጥናቱን ሲከፍቱ እንደገለጹት የህግ የበላይነትን ለማስከበር ህብረተሰቡ በፍትህ ሥርዓት ላይ ጠንካራ እምነት ኖሮት ለውጡን ማገዝ እንዲችል የፍትህ አካላትና የህግ ባለሙያዎች በበለጠ መስራት ይጠበቅባቸዋል።

የህግ የበላይነት ተረጋግጦ የፍትህ ሥርዓቱ አስተማማኝ ደረጃ ላይ ከደረሰ ዴሚክራሲያዊ ሥርዓቱ እንደሚጎለብትና በልማትና በመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴ ውስጥ የተደራጀ የህብረተሰብ ተሳትፎ በበለጠ እንዲጠናከር ያደርጋል ብለዋል

ምልዓተ ሕዝቡ የልማቱ ቀጥተኛ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆንና በአገሪቱ በሁሉም ዘርፍ እየተመዘገበ ያለው ፈጣን ልማትና ዕድገት ቀጣይነት እንዲኖረው በማድረግ ረገድም ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ አመልክተዋል።

በሀገሪቱ ፍትህና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የሕግ በላይነት መከበር ይኖርበታል ያሉት አቶ ብርሃኑ፣ ለዚህም ከተናጠል ይልቅ በተደራጀ መንገድ የሚደረግ እንቅስቃሴ ውጤታማ እንደሚሆን አስረድተዋል።

በህገ መንግሥቱ ለተረጋገጠው የዜጎች የመደራጀት መብት ተፈጻሚነት መንግሥት ፖሊሲዎችንና ሰትራቲጂዎችን አዘጋጅቶ ተግባራዊ በማድረግ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም ተናግረዋል።

የሕግ ባለሙያዎች በተለይ ጠበቆች ሙያው የሚጠይቀውን ሥር-ምግባር ተላብሰው ለህብረተሰቡ በተለይም ለሴቶች፣ ለወጣቶችና ለህፃናትና ነፃ የህግ አገልግሎት ለሚሹ ወገኖች አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ለፍትህ ሥርዓቱ መጎልበት የድርሻቸውን እንደወጡ አሳስበዋል።

የዓውደ ጥናቱ ዓላማ ህግ አውጪ፣ ህግ ተርጓሚና አስፈፃሚ አካለት የፍትህ ሥርዓቱ ተደረሻ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ተቀናጅተ በመስራት ለልማት ዕቅዱ ስኬት ድርሻቸውን እንዲወጡ ግንዛቤ ማስጨበጥ መሆኑን የማህበሩ ፕሬዝደንት አቶ ድሪባ ጋሩምሳ ገልጸዋል።

በዚሁ ዓውደ ጥናት የማህበሩ የ2004 ዕቅድ እንሚጸድቅና በህግ ዙሪያ ጥናታዊ ጹሁፎች ቀርበው በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት እንደሚደረግባቸው መገለጹን የዘገበው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ነው።

About these ads

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Connecting to %s