የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ሰሞኑን ከስብስብነት ወደ ግንባር ለመሸጋገር መወሰኑን አስታውቋል፡፡
መድረክ እንደሚለው አሁን ያለውን የፖለቲካ ሥነ ምኅዳር ለመለወጥ በስድስት ድርጅቶች የተዋቀረውን ስብስብ ወደ ግንባር ማሸጋገሩ የተሻለ እንቅስቃሴ ለማድረግ ያስችለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የተሻለ ዲሞክራሲ ለማስፈንና ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተሻለ አማራጭ ለመፍጠር የሚቻለው ግንባር ሲመሠረት ነው ብሏል፡፡
“እየገዛን ያለው ግንባር [ኢሕአዴግ] ኢትዮጵያን ለሃያ ዓመታት ምን እንዳደረጋት እናውቃለን፤” የሚለው መድረክ፣ “ዋናው ጉዳይ ግንባርን በግንባር መግጠም ነው፤” ብሏል፡፡ የኢሕአዴግን የከፋፍለህ ግዛ ሴራ በማክሸፍ የኢትዮጵያን ሕዝብ በጋራ ዓላማና በጋራ አገራዊ አጀንዳዎች ዙሪያ አቀራርቦና አቻችሎ ለማንቀሳቀስ፣ ግንባር መመሥረቱ የተሻለ ዕድል ይፈጥራል ሲል መድረክ አስታውቋል፡፡
የመድረክ የአመራር አባላት ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና ዶ/ር ሞጋ ሶሬሳ በምስሉ ላይ ይታያሉ፡፡ መድረክ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች አብዛኛውን ምላሽ የሰጡት ዶ/ር መረራ ጉዲና ቃለ ምልልሳቸውን በቃለ ምልልስ ድሕረገጽ ላይ ይመልከቱ፡፡
http://www.ethiopianreporter.com/news/293-news/3763-q-q.html