Benishangul Gumuz ex-president Yaregal apprehended

(Bilisummaa, October 22, 2011) – The Federal Ethics and Anti-Corruption Commission (FEACC) said the former president of the Benishangul Gumuz State, Yaregal Aysheshum, who is suspected in corruption, is put under control on Thursday.

Yaregal was a member of the parliament and also Director-General of the Federal Cooperative Agency (FCA).

The Commission said Yaregal was put under control after the House of Peoples’ Representatives at its 2nd regular meeting of the 2nd tenure held here last Tuesday had stripped his immunity.

According to the Commission, Yaregal is arrested because of misuse of power.

Yaregal was stripped of parliamentary immunity as per the request from the Commission.

The commission said Yaregal embezzled the federal subsidy budget allocated in 1998EC for the construction of the Tana Beles Girls’ Boarding School, Gilgel Beles Teachers’ Training Education College and Assosa Technical and Vocational Training Institute.

The formers state chief was embezzling the public resource with former state education bureau head Habtamu Hika and also with contactors, it said.

The commission said the former state education bureau head, Habtamu Hika and the alleged contactors, who collaborated for the case, are under investigation.

By bilisummaa

የቤነሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዝዳንት የነበረው በቁም እስር ላይ እንደሚገኝ ታወቀ

(ቢሊሱማ,ጥቅምት 22 ቀን 2011)የቀድሞ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የኅብረት ሥራ ማኅበራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ያረጋል አይሸሹም፣ ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ፡፡

አቶ ያረጋል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሁለተኛ ዓመት የሥራ ዘመኑና በሁለተኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ ያለመከሰስ መብታቸውን ያነሳው የሕግ፣ የፍትሕና የአስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙስና ወንጀል መጠርጠራቸውን ጠቅሶ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ባስተላለፈው ሙሉ ድምፅ ነው፡፡

አቶ ያረጋል የክልሉ ፕሬዚዳንት በነበሩበት ጊዜ በክልሉ እንዲሠሩ በጀት ከተያዘላቸው ሦስት ትምህርት ቤቶች ላይ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ጋር በመመሳጠር ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸው በማስረጃ በመረጋገጡና በቂ አመላካች ነገሮች በመኖራቸው ነው ተብሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ያለመከሰስ የሕግ ከለላቸው እንዲነሳ ተወስኗል፡፡

ተጠርጣሪው አቶ ያረጋልን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችለውን የምርመራ ሥራ ለማከናወን በሚመለከተው መንግሥታዊ አካል የቀረበው የሕግ ከለላን የማንሳት ጥያቄ፣ በቋሚ ኮሚቴው ተቀባይነትን በማግኘቱ የሕግ ከለላቸው እንዲነሳ የውሳኔ ሐሳብ መቅረብ መቻሉ በቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ተገልጿል፡፡

By bilisummaa

በአርባ ምንጭ ነዋሪዎችና በወያኔ ዘረኛ አገዛዝ መካከል የተፈጠረው ፍጥጫ አሣሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተሰማ

(ቢሊሱማ,ጥቅምት 22 ቀን 2011) ዘረኛውና ፋሽስቱ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ እያደረሰ ያለው አፈናና ጭቆና ባስመረረው የአርባምንጭና አካባቢዋ ነዋሪዎችና በአገዛዙ መካከል በተነሳው ውዝግብ እስካሁን ወደ 65 የሚጠጉ ሰዎች በመታሰራቸው አካባቢው በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሎአል።

ውጥረቱ ይበልጥ እየተባባሰ የመጣው፤ ከሁለት ሳምንት በፊት በወረዳቸው፣ በዞናቸውና በቀበሌያችው በተንሰራፋው የመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት፣ ለችግር መጋለጣቸውን አዲስ አበባ በመምጣት ለመገናኛ ብዙሀን ይፋ ያደረጉ የአርሶ አደሮች ተወካዮች ለእስር መዳረጋቸውን ተከትሎ ነው።

በመጀመሪያ የታሰሩት፤ አቤቱታ ለማቅረብ አዲስ አበባ የመጡት አቶ ዳሞታ ኡቃ፣ አቶ ዶኮ ኮዶ ፣ አቶ ዳንኤል ዳርዬ እና ሌሎች የቀበሌው ሶስት አርሶ ደሮች ሲሆኑ፤ አሁን ግን የታሳሪዎቹ ቁጥር አስከ 65 እንደሚደርስ ተነግሯል።

“አዲስ አበባ ድረስ ሄዳችሁ ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉዳዩን ተናግራችኋል” በሚል ሰበብ የአካባቢው ፖሊስ አርሶ አደሮቹን ማሰሩን የጠቀሱት ምንጮች፤ እስረኞቹም፤- በላንቴ ፣ በጨንቻ እና በአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ ጣቢያዎች እንደሚገኙ ገልፀዋል።

ምንጮች እንደሚሉት፤ “አለ” በተባለው ችግር ዙሪያ ማጣራት እንዲያካሂዱ ከተመረጡ የአጣሪ ቡድኑ አባላት መካከልም፤ ሁለት የቀበሌው የግብርና ባለሙያዎች ከስራ ታግደዋል። አንዳንድ የላንቴ ቀበሌ ወጣቶችም እስርን በመፍራት ወደ አርባ ምንጭ ከተማ እየሸሹ እንደሆነ ተናግረዋል።

ባለፈው ሳምንት “ስብሰባ ስላለ፤ ፖሊስ ጣቢያ ድረስ መጥታችሁ ተሰብሰቡ” የሚል ትዕዛዝ በየቀበሌው መስተዳድሮች አማካይነት ሲተላለፍ፤ ህብረተሰቡ “መሰብሰቢያ አዳራሽ እያለ ፖሊስ ጣቢያ ግቢ ውስጥ አንሰበሰብም” ማለቱን ተከትሎ በርካታ ሰዎች መታሰር እንደጀመሩ ተዘገቦ ነበር።

በስፍራው የሚንቀሳቀሱት ወኪሎቹን ጠቅሶ ዜናውን የዘገበው ኢሳት እንዳመለከተው የወያኔ ታጣቂዎች በህብረተሰቡ ተወካዮች ላይ የወሰዱት የጅምላ እሰር እርምጃ፤ በአሁኑ ጊዜ ውጥረቱንና ፍጥጫውን እጅግ እንዳባባሰውና ወያኔ እየወሰደ ባለው እርምጃ ያኮረፈው የአካባቢው ህዝብ፤“መልካም አስተዳደር አጥተናል”ለሚለው አቤቱታችን የአገዛዙ ምላሽ እስር ከሆነ፤ ከእንግዲህ የምናደርገውን እናውቃለን“ ማለታቸው ተዘግቦአል

By bilisummaa