የወያኔ አገዛዝ የሁለተኛ ዙር የእስር እቅድ ተጋለጠ

(ቢሊሱማ ዜና, ህዳር 5 ቀን 2011) የወያኔ አገዛዝ ሁለተኛ ዙር የእስር ጥቃቱን በንፁህ ዜጎች ላይ በዋነኛነት በኦሮሞ፣ ኦጋዴንና አማራ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እነዲሁም ተወላጆች ላይ ሊያካሄድ ዝግጅቱን ያጠናቀቀው መሆኑ ታውቅዋል።

የወያኔ አገዛዝ የእስር ጥቃቱን ከሀምሌ ወር 2011 ጀምሮ እየተገበራቸው ካሉት ግዙፍ እኩይ ድርጊቶች ኢምንቱ እነደሆነ የታወቀ ሲሆን ይህም ሀገር ውስጥ የሚገኙ የተቃዋሚ ሀይላትን ከሀገር ጠራርጎ የማውጠት አላማን የተንተራሰ ዘዴ ነው።

መለስ ዜናዊ በቅርቡ በፓርላማ ስብሰባው ላይ በሰጠው መግለጫ መንግስት በርካታ ዜጎች ላይ እስር ለመፈፀም መረጃ እየሰበሰበ እነደሆነ በግልፅ ተናግርዋል፣« ከአሸባሪ ቡድኖች ጋር እየሰሩ ያሉና ግንኙነት ያላቸው ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን፣ ከማሰራችን በፊት ጥቂት ተጨማሪ ማስረጃዎችን ብቻ ነው የምንፈልገው ፣በመቻኮል ሁሉንም ነገር ማበላሸት አንፈልግም» ነበር ያለው።

ይህ ቀጣዮ የጅምላ እስር እቅድ ያነጣጠረው ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ እነዲሁም መረጃን በማቀበል ይሰራሉ ብሎ የጠረጠራቸውን በመንግስት መስራቤቶች ውስት ተቀጥረው የሚሰሩ ሰዎችንና አገዛዙን የሚነፍቁ የመገናኛ ብዙሀኖችንም እነደሚያካትት ታውቅዋል።

የወያኔ አገዛዝ እነኚህን አካላት በትሮጃን ሆርስ ቫይረስ ነው የመሰላቸው፣ የወያኔን አገዛዝ ስራ በማጋለጥ ውድቀቱን የሚያፋጥኑ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ወያኔ በፍትህ ሚኒስተር መስሪያ ቤት አንድ ግብረ አበር ቡድን ያቋቋመ ሲሆን አላማውም በፍትህ መኒስቴር መስሪያቤት ውስጥ በፖለቲካ እስረኞች ላይ የሚደርሰውን ኢሰብአዊ ድርጊትና ስልጣንን በመጠቀም የሚፈፀመውን ወንጀል በተመለከተ ለዜና አውታሮች መረጃዎችን የሚያቀብሉ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ነው።

የውስጥ ምንጮች እንደገለፁት ይሄው ቡድን በዋነኛነት በኦሮሞ የህግ ኤክስፐርቶች ላይ እነዲሁም በአሁኑ ወቅት ወደአሜሪካ ተሰደው የሚገኙት ከዚህ ቀደም የፍትህ ሚኒስተር ዳየሬክተር የነበሩትን የአቶ ለገሰ አለሙ ጉዋደኞች ላይ ያነጣጠረ ነው፣ ይህ ቡድን እነዢህን ግለሰቦች መረጃውን ለዜና አውታሮች ወይም ደግሞ ለአቶ ለገሰ ስለማቀበላቸው በምርመራ መልክ መጠየቃቸውም ታውቅዋል።

ከዚህም ባለፈ “አቶ ለገሰ በኢትዮጵያ መንግስት በጥብቅ የሚፈለግ ግለሰብ ነው፣ ግለሰቡ እጃችን ሲገባ በዚህ ተግባር ከተሳተፋችሁ ለክህደታችሁ ከፍላችሁ የማትጨረሱት እዳ ነው የሚከተላችሁ” የሚል ማስፈራሪያ ከባለስልጣናቱ እንደደረሰባቸውም ገልፀዋል።

ወያኔ ይህን ግብረአበር ቡድን ለማቋቋም የተገደደው ከ ፍትህ ሚነሲተር በተደጋጋሚ ወጥተው በተለያዩ የዜና አውታሮች በታተሙት ሚስጢራዊ ዜናዎች ሲሆን ይህም በኦሮሞዎችና ሌሎችም ግለሰቦች ላይ የሀሰት ክስ በመመስረትና ለእስር በመዳረግ እነዲሁም ቶርች በማድረግ ትልቅ ሚና ሲጫወቱ የነበሩ የወያኔ አባለትን ያጋለጠ በመሆኑ ነው።

By bilisummaa

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) አባላት የ17 ዓመት ጽኑ እሥራት ተፈረደባቸው

(ቢሊሱማ, ህዳር 5 ቀን 2011) በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት በዋና ወንጀል አድራጊነት የተከሰሱት የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) አባላት የኾኑት አብዲወሊ መሐመድ እስማኤል እና ከሊፍ ዐሊ ዳሂር የ17 ዓመት ጽኑ እሥራት ዛሬ ዓርብ ጥቅምት 24 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ተፈረደባቸው፡፡

የከፍተኛው ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ዳኛ ሸምሱ ሲርጋጋ ከሰዓት በኋላ በዋለው ችሎት ላይ እንደተናገሩት ፍርድ ቤቱ ጠዋት በዋለው ችሎት ያደመጠውን የግራ ቀኙን (የዐቃቤ- ሕግ እና የተከላካይ ጠበቃ) የቅጣት አስተያየት አገናዝቦ ተገቢውን ውሳኔ ሰጥቷል፤ የፍርዱ ዓላማ ጥፋተኛውን ማስተማር፣ ኅብረተሰቡን እና አገርን ደግሞ ከጥቃት መከላከል በመኾኑ ወንጀሉን በመካከለኛ ደረጃ መድበነዋል ብለዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን በንባብ ሲያሰማ እንደገለጸው መነሻ ያደረጋቸው አንደኛ እና ሁለተኛ ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት የጸረ ሽብር ሕግ 652/2001 አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ 2 በመተላለፍ ወንጀል መፈጸማቸው በዐቃቤ- ሕግ ማስረጃ መረጋገጡ፣ ሁለቱ ተከሳሾች ከ2000 ዓ.ም እና ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ የኦብነግ አባል በመኾን የጦር መሣሪያ ሥልጠና በመውሰድ እና በመታጠቅ በውጊያ ላይ እስከተማረኩበት ጊዜ ድረስ በሶማልያ ክልል ልዩ ልዩ ዞኖች ኅብረተሰቡን በሽብር ተግባር ማወካቸው እና በዚሁ ተግባር ላይ መኾናቸው ተረጋግጧል፡፡

የአጥፊዎችን የግል ባሕርይ እና አደገኝነት መጠን በማገናዘብ እና የቅጣት አወሳሰን መርህን በማየት ምንም እንኳ የቀረበባቸው ክስ ከ15 ዓመት እስከ እድሜ ልክ ጽኑ እሥራት ወይም በሞት ሊያስቀጣ ቢችልም ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ- ሕግን “ቅጣቱ በከፍተኛ ደረጃ ይያዝልኝ” እና የተከላካይ ጠበቃን ደግሞ “በዝቅተኛ ደረጃ ይያዝልኝ” ጥያቄ ባለመቀበል በመካከለኛ ደረጃ በመውሰድ እያንዳንዳቸው በ20 ዓመት መነሻ ጽኑ ቅጣት በይነን የተከላካይ ጠበቃ ባቀረቧቸው የቅጣት ማቅለያ ነጥቦች ሦስት ዓመት በመቀነስ የ17 ዓመት ጽኑ እስራት እና በወንጀል ሕግ አንቀጽ 23 ሕዝባዊ መብቶቻቸው እንዲሻር ወስነናል፤ ተከሳሾች በውሳኔው ቅሬታ ካላቸው ይግባኝ የመጠየቅ መብታቸው የተጠበቀ ነው ብለዋል፡፡

ዛሬ ጠዋት በዋለው ችሎት ላይ ዐቃቤ- ሕግ እና የተከላካይ ጠበቃ የቅጣት ማክበጃ እና የቅጣት ማቅለያ ነጥቦቻቸውን ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡ ሲኾን ተከሳሾችም የቤተሰባቸውን ኹኔታ በመግለጽ ፍርዱ እንዲቀልላቸው ጠይቀዋል፡፡

ዐቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ወንድማገኝ ባቀረባቸው የፍርድ ማክበጃ ነጥቦች ላይ እንደጠቀሰው በአገሪቱ ሕግ አውጪ ተቋም (ፓርላማ) በሽብርተኝነት በተፈረጀው ኦብነግ ውስጥ በአባልነት በመሳተፍ የመሣርያ ሥልጠና በመውሰድ እና በመታጠቅ በሶማሌ ክልል ዞኖች በለሊት በመንቀሳቀስ ኅብረተሰቡን በማስገደድ በሽብር በማወክ፣ የአገሪቱን መሠረታዊ ተቋማት በማናጋት የክልሉን ሠላም በማደፍረስ ኅብረተሰቡን ሲዘርፉ ነበር፣ በወቅቱ በውጊያ ላይ ሲያዙም በሦስተኝነት እና በአራተኝነት የተከሰሱትን ሲዊዲናውያን ጋዜጠኞች በሕገ-ወጥ መንገድ አገር ውስጥ በመሣርያ አጅቦ በማስገባት ወንጀል የፈጸሙ በመኾናቸው ሌላውንም ለማስተማር በከባድ ደረጃ ወንጀል እንዲያዝልኝ እጠይቃለሁ ሲል ዐቃቤ- ሕግ ጠይቆ ነበር፡፡

የተከላካይ ጠበቃ አቶ ሳሙኤል አባተ በበኩላቸው ዐቃቤ- ሕግ ያቀረባቸው የቅጣት ማክበጃ ነጥቦች በሙሉ በክሱ ላይ የተካተቱ በመኾናቸው ፍርድ ቤቱ ውድቅ እንዲያደርጋቸው ጠይቆ፣ አንደኛ ተከሳሾቹ ግለሰቦች የሚኖሩበት ማኅበረሰብ ዘላን (አርብቶ አደር) ማኅበረሰብ በመኾኑ የአኗኗር ኹኔታቸው ተጽዕኖ ስላለው ከግንዛቤ እንዲገባ፣ ሁለተኛ ምንም ዐይነት መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ትምህርት የሌላቸው በመኾኑ የርዕዮተ ዓለማዊ ኹኔታዎችን ለመረዳት ስለሚከብዳቸው በቀላሉ ለኦብነግ ዓላማ መልማዮች የሚጋለጡ መኾናቸው ታሳቢ እንዲኾን፣ ሦስተኛ ድርጊታቸውን ከመጀመሪያው ምርመራ ጀምሮ ያልካዱ መኾናቸው እና ከዚህ በፊት በምንም ዐይነት ወንጀል ተከሰው የሚያውቁ ሰዎች ባለመኾናቸው እና ዐቃቤ- ሕግም ይህን ባለማሳየቱ ከዚህ ቀደም ሕይወታቸው ሰላማዊ ሰዎች እንደነበሩ ስለሚያመላክት ፍርድ ቤቱ የቅጣቱን መነሻ እርከን 15 ዓመት በማድረግ የቅጣት ማቅለያውን ታሳቢ በማድረግ ከ7 እስከ 9 ዓመት ቢቀጣቸው ሊያስተምራቸው ይችላል፤ የቅጣት ዓላማውም ማስተማር ነውና ብሏል፡፡

የመጀመሪያ ተከሳሽ አብዲወሊ መሐመድ እስማኤል የማቅለያ ሐሳቡን ፍርድ ቤቱ በአስተርጓሚ በኩል ሲጠይቀው እኔ የ7 ልጆች አባት፤ የሁለት ሚስቶች አባወራ እና ቤተሰብ አስተዳዳሪ ነኝ ፣ አሁን በምን ኹኔታ ላይ እንዳሉም አላውቅም፣ ምንም ዐይነት ሀብት የላቸውም ብሏል፡፡ ሁለተኛው ተከሳሽ ከሊፍ ዐሊ ዳሂር በበኩሉ ቀለል ባለ መንፈስ በአጭር ቋንቋ ልጆች የሉኝም ሚስት እና ቤተሰብ ግን አለኝ ብሏል፡፡

የመሀል ዳኛ ሸምሱ ሲርጋጋ ዐቃቤ-ሕግ በአብዛኛው ያቀረባቸው ቅጣት ማክበጃዎች በክሱ ላይ እንደተካተተ ጠቅሰው፣ ተከሳሾቹ በሌሊት ሲንቀሳቀሱ ነበር የተባለው ማንኛውም ወንጀለኛ ቀንም ኾነ በሌሊት ስለሚንቀሳቀስ ምንም የተለየ ነገር ስለሌለው ውድቅ መደረጉን፣ የአሸባሪ ቡድኑ ጋር ስምምነት አድርገዋል የሚለውም ለማክበጃ እንደሚያገለግል ኾኖ አላገኘነውም፡፡

በሌላ በኩል የተከሳሽ ጠበቃ ያቀረቡት የተከሳሾቹ የኑሮ ዘዬ፣ ኹኔታ፣ የቤተሰብ መሪ መኾናቸው፣ ትምህርት አለመማራቸው ታሳቢ ተደርጎ እና ከዚህ ቀደም ምንም ተከሰው የማያውቁ መኾናቸው አሊያም ከዚህ ቀደም የነበራቸውን ባሕርይ ዐቃቤ- ሕግ በማስረጃ ባለማሳየቱ የቅጣት ማቅለያውን ተቀብለነዋል፡፡

ስለዚህ አንደኛ እና ሁለተኛ ተከሳሾች በመካከለኛ ደረጃ ወንጀል 20 ዓመት ጽኑ እሥራት የሚቀጡ ቢኾንም እስከ አሁን የታሰሩት ታሳቢ ተደርጎ 17 ዓመት ጽኑ እሥራት እንዲቀጡ ወስነናል፤ በውጊያ ላይ ሲያዙ ታጥቀውት የነበረው ሁለት ክለሽንኮቭ መሣርያ ለመንግሥት ውርስ እንዲኾን፣ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 23 በእሥር ላይ በሚቆዩበት ጊዜ የመምረጥ እና የመመረጥ ሕዝባዊ መብቶቻቸው እንዲሻር ወስነናል በማለት 10፡30 ሰዓት ላይ ችሎቱ ተበትኗል፡፡

By bilisummaa